The European Union Opposes Tensions in the Region and the Forced Roundup of Youth
As residents report renewed forced military recruitment in Tigray, the European Union and the United States warn that political and security developments in the region risk violating the Pretoria agreement and deepening the humanitarian crisis, while TPLF officials deny the accusations.

Monday, Sene 22, 2018 E.C. The European Union has objected to the tension in the region and to the forced roundup of young people. Officials of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), which has no legal recognition from the National Election Board of Ethiopia or from Ethiopia’s federal government, are dismissing what has been described as compulsory military roundup as a mistaken judgment.
ሰኞ፣ ሰኔ 22 2018የአውሮፓ ህብረት በክልሉ ያለውን ውጥረትና የወጣቶች የግዳጅ አፈሳን ተቃውሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ህጋዊ እውቅና የሌላቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለስልጣናት ግን አስገዳጅ የተባለውን ወታደራዊ አፈሳ የተሳሳተ ፍረጃ በማለት እያጣጣሉት ነው
Residents say that what has been described as the forcible roundup of young people for war is continuing in the Tigray region. The European Union has objected to the tension in the region and to the forced roundup of youth. Officials of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), which has no legal recognition from the National Election Board of Ethiopia or from Ethiopia’s federal government, are dismissing what has been called compulsory military roundup as a mistaken judgment. The alleged compulsory roundup for war taking place in the region
በትግራይ ክልል አስገዳጅ የተባለው የወጣቶች የጦርነት አፈሳ መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት በክልሉ ያለውን ውጥረትና የወጣቶች የግዳጅ አፈሳን ተቃውሟል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ህጋዊ እውቅና የሌላቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለስልጣናት ግን አስገዳጅ የተባለውን ወታደራዊ አፈሳ የተሳሳተ ፍረጃ በማለት እያጣጣሉት ነው፡፡ በክልሉ እየተከናወነ ነው የተባለው አስገዳጅ የጦርነት አፈሳ
According to a young commentator who lives in Mekelle, in the Tigray region, and who was formerly a member of the Tigrayan forces, although he left the army because of an injury he sustained during the war several years ago, he is now being compelled to return to military service. The former young combatant, who asked that his name not be used out of concern for his safety, said that both through the office where he works and through the kebele where he lives, he has been ordered to rejoin the army by force, and that he is now in hiding. “An order has now been issued against me both through my workplace and through the kebele,” the young man said, explaining that the roundup of young people for war is being carried out in different forms.
በትግራይ ክልል የመቀለ ከተማ ነዋሪ የሆነና የቀድሞ የግራይ ኃይሎች ሰራዊት አባል የነበረ አስተያየት ሰጪ ወጣት እንደሚለው፤ እሱ ከአመታት በፊት በጦርነቱ ወቅት ባስተናገደው ጉዳት ጦሩን ለቆ ብወጣም በአስገዳጅ ወደ ጦሩ አባልነት እንደሚመለስ እየተገደደ ነው፡፡ ለደህንነቱ በመስጋት ስሙ እዳይጠቀስ ጠይቆ አስተያየት የሰጠው የቀድሞ ተዋጊው ወጣት፤ በሚሰራበትም መስሪያ ቤት ሆነ በሚኖርበት ቀበሌ በኩል በአስገዳጅነት ዳግም ጦሩን እንዲቀላቀል መጠየቁን አስታውቆ በመሸሽ እንዳለም ገልጿል፡፡ “እኔ አሁን በመስሪያ ቤቴም ሆነ በቀበሌ በኩል ትዕዛዝ ወጥቶብኛል” የሚለው ወጣቱ፤ የወጣቶች የጦርነት አፈሳ በተለያዩ መልኮች እየተፈጸሙ እንደሚገኙም አስረድቷል፡፡
According to the young man, the present situation in the Tigray region is alarming, and war appears to have become unavoidable. “Here, now, war is inevitable,” he said, while also explaining that residents of the region are trying in various ways not to buy into the idea of war. The former combatant said that any war that might break out now would by no means receive the support of the region’s youth as the previous one did; in his view, there is no sufficient reason that would justify going to war. As a result, he says, young people are leaving the region by whatever means they can find. The European Union’s warning
ወጣቱ እንደሚለው በትግራይ ክልል አሁናዊው ሁኔታ አስጊና የጦርነቱ መከሰት ኤቀረም መስሏል፡፡ “እዚህ አሁን ጦርነቱ አይቀሬ ነው” በማለትም ወጣቱ የክልሉ ነዋሪ ግን የጦርነቱ ሃሳቡን ላለመግዛት በተለያዩ መንገዶች ጥረቶች ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡ አሁን ሊነሳ የሚችለው ጦርነት እንደቀድሞው ፈጽሞ የክልሉን ወጣት ድጋፍ የሚያገኝ አይሆንም የሚለው የቀድሞ ተዋጊው፤ ለዚህም ደግሞ ለጦርነት የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለመኖሩን በአስተያየቱ አመልክቷል፡፡ በመሆኑም ወጣቱ ባገኘው መንገድ ከክልሉ እየወጣ ነው ይላልም፡፡ የአውሮፓ ህብረት ማሳሰቢያ
Meanwhile, the European Union too is expressing concern over the current situation in Tigray. The United States government had previously said it was concerned by what it described as violations of the Pretoria cessation-of-hostilities agreement in Tigray, and urged the region’s administrations to return to the framework of that agreement.
ይህ በእንዲህ እናዳለ የአውሮፓ ህብረትም በትግራይ አሁናዊ ሁኔታ ስጋቱን እየገለጸ ነው፡፡ የአሜሪካ መንግስት ከዚህ ቀደም በትግራይ እየተጣሰ ነው ያለውን የፕሪቶሪያ የግጭት ማስቆም ስምምነት መጣሱ አሳስቦናል በማለት የክልሉ መስተዳድሮች ወደ ስምምነቱ መስመር እንዲመለሱ ሲል አሳስቧል፡፡
In an official statement issued on the concerns it says it has observed regarding political and security matters in the Tigray region, the Union’s delegation in Ethiopia urged the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) and the Ethiopian federal government to return to implementing the Pretoria cessation-of-hostilities agreement they signed roughly four years ago.
የህብረቱ የኢትዮጵያ ልዑክ በትግራይ ክልል እየተስተዋለ ነው ያለውን የፖለቲካ እና ፀጥታ ጉዳዮች ስጋትን በማስመልከት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ከአራት አመታት ግድም በፊት ወደ ፈረሙት የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር እንዲመለሱ አሳስበዋል፡፡
In its statement, the Union’s delegation said, “We are concerned by the tensions being seen in northern Ethiopia.” The Union also criticized what it said was the establishment of a parallel government in Tigray, calling it a clear violation of the Pretoria agreement. This European Union warning, which follows a similar statement previously issued by the United States, says there is grave concern that preparations for war could worsen the humanitarian crisis in the Tigray region. The Union also indicated that it would work with the African Union and the United States to ensure lasting peace in the region.
የህብረቱ ሉዑክ በመግለጫው “በሰሜን ኢትዮጵያ እየታየ ባለው ውጥረት ስጋት ገብቶናል” ነው ያለው፡፡ ህብረቱ በትግራይ እየተመሰረተ ነው ያለው የትይዩ መንግስት ግልጽ የፕሪቶሪያው ስምምነት ጥሰት ነው ሲል ተችቷልም። ከዚህ በፊት አሜሪካ አውጥታ ከነበረው ተመሳሳይ ይዘት ካለው መግለጫ ተከትሎ የመጣው ይህ የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያው፤ የጦርነት መሰናዶው በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ እንዳያባብሰው እጅጉን የሚሰጋ ነው ይላል፡፡ ህብረቱ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንም ከአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ስቴትስ ጋር እንደሚሰራ አመልክቷል፡፡
It will be recalled that the United States also recently voiced opposition over what it described as a law issued in the region that tramples on human rights, as well as over compulsory military recruitment and other concerns in the region. But Ato Mikael Asgedom, spokesperson for the TPLF, which has not received recognition from the National Election Board of Ethiopia and which recently formed a regional government that is not regarded by the federal government as a legal government, denied all the accusations leveled against it in his response to Deutsche Welle. In his remarks, the TPLF official objected to the claims, saying, “The accusations being made regarding the recently issued law, as well as regarding the forced roundup of young people, are baseless.” Siyum Getu, Hirut Melesse, Azeb Tadesse
አሜሪካም በቅርቡ በክልሉ ሰባዓዊ መብቶችን የሚደፈጥጥ የተባለው ህግ በመውጣቱ እና በክልሉ አስገዳጅ የጦርነት ምልመላ እንዲሁም ስጋቶችን በማስመልከት ተቃውሞ ማሰማቷ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያላገኘውና በፌፌራሉ መንግስትም እንደ ህጋዊ መንግስት የማይታየውን በቅርቡ የክልል መንግስት የመሰረተው የሕወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሚካኤል አስገዶም ግን የሚቀርቡባቸውን ሁሉንም ክሶች አስተባብለው ነው ለዶይቼ ቬለ ምላሽ የሰጡት፡፡ የህወሓት ባለስልጣኑ በአስተያየታቸው፤ “በቅርቡ የወጣው ህግን በተመለከተም ሆነ የወጣቶች አስገዳጅ አፈሳን በተመለከተ የሚቀርቡባቸው ክሶች መሰረተብስ ናቸው” በማለት ተቃውመው ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ሥዩም ጌቱ ኂሩት መለሰ አዜብ ታደሰ